አዳነ የኔነህ፣ ዳንኤል ወርቅነህ እና ቅድስት ድጋፌ የተባሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የስዕል ኢግዚቢሽን እኤአ ከሴፕቴምበር 25-29 ቀን 2014 ድረስ በማዘጋጀት በጄኔቫ ለተመልካች ዕይታ አቅርበዋል።

በኢግዚቢሽኑ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት በስዊዘርላንድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደርና በተ.መ.ድ ቋሚ መልእክተኛ ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው አርቲስቶቹ በጋራ በመሆን ስራዎቻቸውን ለተመልካች ዕይታ ማቅረባቸው ከስዕሎቻቸው ባሻገር አገራችንን ለማስተዋወቅና በጎ ገፅታዋን ለማሳየትም እንደሚያስችል እምነታቸው እንደሆነ ገልፀዋል ። ኤግዚቢሽኑ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ የዳያስፖራ አባላትን ለመሰል ተሳትፎ የሚያበረታታ ከመሆኑ አኳያ የአርቲስቶቹን ተነሳሽነት አድንቀዋል ።

በዕለቱ አርቲስቶቹ ያቀረቧቸውን ስዕሎች በተመለከተ ለጎብኝዎች ገለፃ አድርገዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook