በኢፌዲሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 13-17 ቀን 2024 ድረስ በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው 149ኛዉ የዓለም አቀፋ የፖርላማ ህብረት ስብሰባ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

ህብረቱ በዚህ ጉባኤው በሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI)፣ሰላምና ፀጥታን በማስፈን ዙሪያ እና የዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ማጎልበት በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ዙሪያ በመምከር ዉሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። በተጨማሪም ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች መፍትሄ ለማመላከት እና በፓርላማ ደረጃ ሊተገበሩ የሚችሉ የትብብር መፍትሄዎችን ለመፈተሽ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ዙሪያም ይመክራል።

የኢትዮጵያ ተሳትፎ አገሪቱ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ትብብሯን ይበልጥ ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል። የልዑካን ቡድኑ በቆይታዉ በዘርፋ የአገራችንን ልምድ በተመለከተ ተሞክሮውን እንደሚያካፍልም ይጠበቃል።

የአለም አቀፋ የፖርላማ ህብረት ጉባኤ በዓለም ዙሪያ ላሉ የፓርላማ አባላት ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ለመወያየት እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር መድረክ መሆኑ ይታወቃል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook