ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው ለክቡራን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የልኡካን ቡድን በጄኔቫ አቀባበል አድርገዋል።

በወቅቱ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ በመላ አገሪቱ እያካሄደ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተመለከተ ክቡራን ኮሚሽነሮቹ ለክቡር አምባሳደሩ መረጃ አጋርተዋል።

በልኡካን ቡድኑ ውስጥ ክቡር ኮሚሽነር ዶ/ር አምባዬ ኡጋቶ፣ ክቡር ኮሚሽነር ዘገዬ አስፋው ፣ ክቡር ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም፣ ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ሙሀመድ ድሪር እንዲሁም ክቡር ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ ይገኙበታል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook