ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ በግል መገልገያ ዕቃዎች መመሪያ ቁጥር 923/2014 መሰረት እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች
- እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ፡፡
- ለግል መገልገያ እንዲዉሉ ወደ አገር የሚገቡ ወይንም ከሃገር የሚወጡ ዕቃዎችን ለመወሰን በወጣ መመሪያ ቁጥር 923/2014 መሰረት፣ ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡ፣ የግል መገልገያ ዕቃዎች ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ።
አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ
- ፓስፖርት ወይንም ሌላ የጉዞ ሰነድ
- አንድ አመትና ከዚያ በላይ ዉጭ ሃገር የኖረ መሆኑን የሚያሳይ ከሃገር ሲወጣና ወደ ሃገር ሲመለስ አግባብ ባለዉ የመንግስት አካል በፓስፖርቱ ላይ የሰፈረ ማረጋገጫ ወይም በሚኖርበት አገር ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ወይንም ቆንስላ ጽ/ቤት የተሰጠና በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ማስረጃ፤
- ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ከዘጠና ቀናትና በላይ አገር ዉስጥ ያልቆዬ/ች ስለመሆኑ የሚቀርብ ማስረጃ
- የእቃዎች ዝርዝርና ዋጋ መግለጫ
- እቃዉ ከአንድ አመትና ከዚያ በላይ ያገለገለ ስለመሆኑ በባለመብት የቀረበ ማረጋገጫ
- ከስደት ተመላሾች ከስደት ተመላሽ ስለመሆናቸዉ የሚያረጋግጥ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል የቀረበ ማስረጃ
- በ ስዊዘርላንድ፣ ኦስትሪያ፣ ሮማንያና ሃንጋሪ ነዋሪ መሆንዎን የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ
- መጠየቂያ ቅጽ መሙላት