በጄኔቫ የኢፌዲሪ መንግስት ቋሚ ተጠሪ ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ከሚሰሩ ፕሮፌሽናል የዳያስፖራ አባላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል::
በክቡር አምባሳደሩ መኖሪያ ቤት በተደረገው በዚህ የትውውቅ ፐሮግራም በጄኔቫ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሰሩ የዳያስፖራ አባላት ተገኝተዋል ::
ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ ከባለሙያዎች ጋር በመተዋወቃቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። የዳያስፖራ አባላቱ በሙያቸው፣ በልምዳቸውና በገንዘባቸው በተለያየ መንገድ ለትውልድ አገራቸው እስካሁን ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ይሄው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው የፀና መሆኑን በመግልፅ የሚሲዮኑ ድጋፍ እንደማይለያቸውም ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ በዚህ ውቅት አረጋግጠዋል።
የዳያስፖራ አባላቱ በበኩላቸው ስለተዘጋጀው የትውውቅ መድረክ ምስጋናቸውን በመግለፅ እንደከዚህ በፊቱ አገራቸውን በሚችሉት ሁሉ ለማገዝ ዛሬም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህ የትውውቅ መድረክ ከሚሲዮኑ መሪ በተጨማሪ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ያኒት አበራና ሌሎች በቅርቡ የተመደቡ ዲፕሎማቶችም ከዳያስፖራ አባላቱ ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook