የኢፌዲሪ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ጄኔቫ በሚገኘዉ የኢፌዲሪ ሚሲዮን በመገኘት ከሰራተኞች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት አድርገዋል።

የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ ከበበዉ በሚሲዮኑ እየተከናወኑ በሚገኙ ዋና ዋና የባለብዙ መድረክ እና የሁለትዮሽ ግንኙነት የዲፕሎማሲ ስራዎች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል። ገለፃዉን ተከትሎ ከሚሲዮኑ ስራ ጋር በተያያዘ ከሰራተኞች አስያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተዋል።

ክቡር ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ በበኩላቸው በሚሲዮኑ ሰራተኞች በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ በመሰጠት በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook