ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

የዚህን ጥሪ ሶስተኛ ምዕራፍ ተከትሎ ከስዊዘርላንድ የሄዱ ሁለተኛ ትውልድ ወጣት የዳያስፖራ አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። በጫካ ፕሮጄክት የሚከናወኑ የልማት እና የኮሪደር ስራዎችንም ጎብኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የወጣቶቹ ወላጆች ተገኝተዋል::

ጥሪውን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት ለሚሄዱ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የተዘጋጁና ይፋ የተደረጉ መርሀ ግብሮች እስከ ጥቅምት መጀመሪያ ድረስ የሚቀጥሉ መሆኑ ይታወቃል::

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook