ዻጉሜ 2 ቀን 2016 ዓም የአዲስ ዓመት ዋዜማን ምክንያት በማድረግ በጀኔቫ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የዳያስፖራ መድረክ ላይ ለህዳሴዉ ግድብ ግንባታ 17, 000 /አስራ ሰባት ሺህ/ የስዊዝ ፍራንክ የቦንድ ግዥ ቃል ተገብቷል።

የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው አዲሱ ዓመት ለተሻለ ለውጥና ለአዲስ ተስፋ ራሳችንን የምናዘጋጅበት እንዲሁም በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ የምንሰራበት ሊሆን ይገባል ሲሉ በመድረኩ ለተገኙ የዳያስፖራ አባላት መልእክት አስተላልፈዋል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ መንግስት በቅርቡ ይፋ ባደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ መሰረት በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተግባራዊ መደረጉ ዳያስፖራው ገንዘቡን በህጋዊ መንገድ መላክ እንዲችል የሚያበረታታ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ተከትሎ ቀሪውን የግንባታ ስራ ለማጠናቀቅ ዳያስፖራው ድጋፉን እንዲያደርግ በቀረበው ጥሪ መሰረት በመድረኩ ከተሳተፋ የዳያስፖራ አባላት የ 17,000 የስዊዝ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ለመፈፀም ቃል ገብተዋል።

በእለቱ ለስራ ጉዳይ በስዊስዘርላንድ የተገኙት ክቡራን የአገራዊ ምክክር ኮምሽን ኮምሽነሮች በኮሚሽኑ ተልዕኮና እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል። ገለፃውንም ተከትሎ ከዳያስፖራው ለተነሱ ተያያዥ ጥያቄዎች ተጨማሪ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook