Diaspora Overviews

ኢትዮጵያ በዳያስፖራ ጉዳይ ላይ ልዩ ትኩረት አድርገው ከሚሰሩ አገሮች የምትመደብ ነች፡፡ ኢትዮጵያ እንደሌሎች ሀገራት ሁሉ የዳያስፖራውን ጉዳይ በልዩ ትኩረት እንድትይዘው የሚያደርጓት በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ሶስት ነጥቦችን በዋናነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

1ኛ. መንግስት ዜጎቹ በሀገርቤትም ሆነ በውጭ ሀገራት በሚኖሩባቸው ግዚያት በነርሱ ላይ ያለበትን ግዴታ ለመወጣት ካለበት ኃላፊነት የሚመነጭ ይሆናል፡፡

2ኛ. በአለምአቀፍ ደረጃ ሰፊ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው በሀገራት ልማት እና ዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ‹‹ የዳያስፖራው አማራጭ›› ወይንም “The Diaspora Option” በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚቆጠር በመሆኑ ነው፡፡ የዳያስፖራ አማራጭ በሀገር ልማት እና የመልካም አስተዳደር ግንባታ ላይ ከዳያስፖራው የሚኖርን ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ በተቀናጀ መልኩ አስተባብሮ መጠቀምን መርሁ ያደረገ አሰራር ነው፡፡

3ኛ. እራስን የአለምአቀፍ ማህበረ ፖለቲካዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ መሄድ አስፈላጊ መሆኑ ነው፡፡ ሉላዊነት  በፈጠረው ድንበር ተሸጋሪ የዜግነት ፅንሰ ሀሳብ፣ የማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋትና የሀሳብ ፍሰት መጨመር፣ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ትውልድ ማህበረ ፖለቲካዊ እሳቤ እየተቀየረ መምጣት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ከአገራቸው ጋር የማስተሳሰሩ ስራ አለምአቀፍ ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ የሚያደርግ ስራ የሚጠይቅ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲም እነዚህን ሀገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ሁኔታዎች ታሳቢ ባደረገና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰባችንን እንደ ማህበረሰብ የሚረዳበትን እሳቤ በመቅረፅ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ተዋቅሯል፡፡

የኤጀንሲው የዳያስፖራ ማህበረሰብ እሳቤ

የዳያስፖራ ማህበረሰቡን የምንረዳበት እና የምንገልፅበት  መንገድ ዳያስፖራውን በአገሩ ልማት እዲሳተፍ እና መንግስም የዳያስፖራው መብት እና ጥቅም ለማስከበር የሚያደርገውን ጥረት በአይነትም በመጠንም ተፅእኖ ያሳድርበታል፡፡ በአጠቃላይ ኤጀንሲው በአራት መርሆዎች ላይ የተመሰረተ የዳያስፖራ ማህበረሰብ እሳቤን ይዞ ይንቀሳቀሳል፡፡

  1. የኢትዮጵያ ዳያስፖራስን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ ወይንም በማህበራዊ ጉዳዮች ምክንያት ከሀገራቸው ወጥተው በየትኛውም የአለማችን ክፍል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በአመለካከትም በተግባርም የሚያጠቃልል ነው፡፡
  2. የዳያስፖራ ማህበረሰባችንእንደዜጋመብትእናጥቅምእንዳሉትሁሉየዜግነትኃላፊነትምአለበት፡፡በተለይም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በሀገሩ ጉዳይ ላይ እንዲሳተፍ የሚያደርጉት ስነልቦናዊ ሀገራዊ ትስስርን እንደመልካም አጋጣሚ በጠቀምና በማዳበር ዳያስፐራው የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የሚያደርጉ አስተሳበሰቦችና አሰራሮችን ኤጀንሲው የሚከተልይሆናል፡፡
  3. ኤጀንሲው የዳያስፖራ ማህበረሰባችን በሀገራዊ አንድነት ጥላ ስር ነገር ግን በሀገር ቤት ከሚኖሩ ዜጎች የተለየ ማህበረሰባዊ መዋቅር፣ ማህበረ-ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጨባጭ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝና ለዚህ በሚመጥን አስተሳሰብ፣ አሰራር እና መዋቅር ሊስተናገድ እንደሚገባ መነሻ ያደረገ የዳያስፖራ ማህበረሰብ እሳቤ አለው
  4. የዳያስፖራ ማህበረሰባችን በአመለካከቱ እና በአቋሙ ሳይሆን በዜግነቱ እና በትውለደ ኢትዮጵያዊነቱ አቃፊ የሆነ ዘላቂ በጎ ምስል እንጂ በግዚያት እና በሁኔታዎች ተለዋዋጭ የሚሆን የደጋፊ እና ነቃፊ መገለጫዎች ኤጀንሲው የሚከተል አይሆንም፡፡
  5. የዳያስፖራ ማህበረሰባችን በውጭ ሀገራት የሚኖር ቢሆንም በሀገር ቤት የሚኖረውን መብት፣ ጥቅም እና ሀገራዊ አበርክቶ በሀገር ውስጥ ለማሳካት የሚደረገው ጥረት ግን በሀገር ቤት ከሚኖረው ዜጋ ጋር በቀጥታ የሚያገናኘው በመሆኑ መልካም መስተጋብርን ለማሳደግ የሚያስችል የማህበረሰብ እሳቤ ኤጀንሲው ይከተላል፡፡

የኢትዮጵያ ዲያፖራ ኤጄንሲ አገልግሎትን በተመለከተ ቋሚ መልእክተኛ ጽ/ቤታችንን በስልክ ቁጥር (+41 22 919 70 10/12) ወይንም በአካል በመምጣት ማግኘት ይችላሉ።

 

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ድረ ገጽን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook